በቤት ውስጥ ፈሳሽ ሳሙና አሰራር: ቅደም ተከተሎች
ፈሳሽ ሳሙና በቤት ውስጥ ለማዘጋጀት ፓታስየም ሃድሮ ኦክሳይድ ( potassium hydroxide) ዘይቶችን (ኮከነት ዘይት ፣የጉሎ ዘይትወይም ሌላ ዘይት) እና የተጣራ ወይም የዝናብ ውሃ አስፈላጊ ነው። የሚከተሉትን ዝርዝር ቅደም ተከተሎች በመጠቀም ፈሳሽ ሳሙናን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዴት እንደሚሰራ ዝርዝር መመሪያ ያገኛሉ።
Step 1: ንጥረ ነገሮችን ያሰባስቡ
ፈሳሽ ሳሙናን ለማዘጋጀት የሚከተሉትን ንጥረ ነገሮች ያስፈልግዎታል።
- የተጣራ ውሃ
- ፖታስየም ሃይድሮክሳይድ
- ዘይቶች (ለምሳሌ የወይራ ዘይት፣ ኮኮናት ዘይት፣ ካስተር ዘይት)
- ሽታ ለመጨመር ሽታ ያላቸው ዘይቶች፣ለምሳሌ የጥቁር አዝሙድ ዘይት (መጨመር ከፈለጋችሁ ብቻ)
- ግሊሰሪን (ጨመር ከፈለጋችሁ ብቻ)
Step 2: የደህንነት ጥንቃቄዎችን ይውሰዱ
ሁልጊዜም ሲሰሩ የመከላከያ ልብሶች፣ ጓንቶች እና የዓይን መከላከያዎችን መልበሶን ያረጋግጡ።
Step 3: ፖታስየም ሃይድሮክሳይድን ከውሃ ጋር መቀላቀል
የፖታስየም ሃይድሮክሳይድን በዝግታ ወደ የተጣራ ውሃ ውስጥ ይጨምሩ። ሙሉ በሙሉ እስኪሟሟ ድረስ በዝግታ ይቀላቀሉ።
Step 4: ዘይቶችን ፈሳሽ እስኪሆኑ ድረስ ያሙቁ
ዘይቶቹን በማሞቅ (ከ60°C ወደ ታች ) ሙሉ በሙሉ ፈሳሽ እስኪሆኑ ድረስ ይጠብቁ።
Step 5: ፈሳሽ ፖታስየም ሃይድሮክሳይድን ከ ዘይቶች ጋር ይቀላቀሉ
ፈሳሽ ፖታስየም ሃይድሮክሳይድን ወደ ዘይቶችን በመቀላቀል ሳያቋርጡ በፕላስቲክ ማንኪያ ያማስሉ። ውህዱ እስኪወፍር (ሳፓኒፋይድ) ድረስ ማማሰሎን አያቋርጡ።
Step 6:ፈሳሽ ሳሙናውን በውሃ በማቅጠን ያዘጋጁ
የተጣራ ውሃን ወደ ሳፖኒፊድ ሳሙና ውስጥ ይጨምሩ እና እስከ ሚፈልጉት ድረስ ያቅጥኑት። ይህ ሂደት ብዙ ሰዓታት ስለሚወስድ ትዕግስት ይኑርዎት።
Step 7: ሽታ እና ቀለም ይጨምሩ
ሳሙናው ሙሉ በሙሉ ፈሳሽ ከሆነ በኋላ አስፈላጊ ሽታ ያላቸው ዘይቶችን እና ቀለሞችን በተጨማሪ ማከል ይችላሉ። የሚፈልጉት ሽታ እና ቀለም እስኪይዝ ድረስ በደንብ ይቀላቀሉ።
Step 8: በመጨረሻም በሚያማምሩ ጠርሙሶች ያሽጉ
ፈሳሽ ሳሙናውን እስኪቀዘቅዝ ድረስ ያቆዩት፣ ከዚያም ወደ ንፁህ ጠርሙሶች ወይም ማከፋፈያዎች ይጨምሩት።
በቤት ውስጥ የተሰራው ፈሳሽ ሳሙናዎ ለመጠቀም ወይም ለገበያ አሁን ዝግጁ ነው!
No comments:
Post a Comment